በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው ።
ፈጣሪ በእስልምና አስተምሮ አንድ ብቻ የሆነ ያለና ሁልም የሚኖር ዘላለማዊ ሕያው የሆነ ሁሉን አዋቂ ፣ ጥበበኛ ፣ ሰማያት እና ምድርን ፤ መላዓክትን ፣ አደምን እና ሃዋን የፈጠረ እንዲሁም ታላላቅ ነቡያትን እና መልክተኞችን ያስነሳ ለመረጣቸውም ነብዮች መጸሀፍትን የሰጠ ነው።
በተጨማሪም ፈጣሪ ፈጽሞ አምሳያ የሌለው ነው፡- አላህ ፈጣሪና አምላክ ነው፡፡ ከሱ ውጭ ያለው በጠቅላላ ፍጥረትና ባሪያዎች ናቸው፡፡ አላህ ፍጡሩን አይመስልም፡፡ ፍጡራንም አላህን አይመስሉም፡፡ ስለዚህ የአላህን ፍጹማዊ የ ጌትነት ባሕሪውን ከማጽደቅ ውጭ ከፍጡራን ውስናዊና ጊዜያዊ ባሕሪ ጋር አናመሳስለውም፡፡ በባሕሪያቱ ሞክሼና ብጤ የማይገኝለት፣ ፍጹማዊ አንድነት ያለው አምላክ ነው፡፡ ይህንን የበለጠ የሚያስረዱ አንቀፅችን ከ ቁርአን እንመልከት
ምዕሪፍ 6 አንቀፅ 102

ምዕሪፍ 4 አንቀፅ 1

ምዕሪፍ 4 አንቀፅ 63

ምዕሪፍ 25 አንቀፅ 58

ምዕሪፍ 19 አንቀፅ 65

ምዕሪፍ 112 አንቀፅ 4

በ እስልምና ጣዋት አምልኮ ሽርክ ይባላል ማጋራት እንደማለት ነው በፈጣሪ ላይ ማጋራት በእስልምና ከሁሉም ሀጥያቶች መካከል ትልቁ ሀጥያት ሲሆን ከፈጣሪ ምህረትን ሳይጠይቅ የሞተ ሰው ለ ጀሀነብ እሳት ቅጣት ያዳረጋል።
ምዕሪፍ 4 አንቀፅ 48

ምዕሪፍ 16 አንቀፅ 36

ምዕሪፍ 4 አንቀፅ 36

ስለዝህ በግልፅ እንተመለከትነው ከ አንዱ እና ከ እውነተኛ አምላክ ውጪ ለሆኑ ጣዋታትንም ይሁን ምንንም እና ማንንም ማምለክ በእስልምና ከሁሉም ሀጥያቶች መካከል ትልቁ ሀጥያት እንደሆነ እና ከፈጣሪ ምህረትን ሳይጠይቅ የሞተ ሰው ለ ጀሀነብ እሳት ቅጣት እንዳሚዳረግ ነው።
በኢስላም በጣም መሠረታዊ የሆነው አስተምህሮት ሁሉን ቻይ በሆነው አላህ ማመን ፣ እና እርሱ የአጽናፈ ዓለሙ ብቸኛ ፈጣሪ እና ጠባቂ መሆኑን መገንዘብ እንዲሁም ሌሎች ሁሉ-ነቢያትም ፣ መላእክትም ወይም ‹ቅዱሳን› የሚባሉትን ጨምሮ ጥገኛ እና ፍጡራን እንድሆኑ መገንዘብ ከአላህ በስተቀር ማንም ችሎታም ፣ ኃይልም የሌለው መሆኑን መረዳት ነው ያንተን ፅሎት ለመስማት ስዕል ወይም ድንጋይ እንተማያስፈልገው መረዳት ነው።
በ እስልምና አስተምህሮ የሰው ልጆች እንድ እና እውነተኛ ከሆነው ከፈጣሪያቸው ጋር ካለምንም ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብተኝነት ቀጥትኛ የሆነ ግንኙነት ነው ያላቸው ብሎ ነው የሚያስተምረው።
ምዕራፍ 2: አንቀጽ 186

ምዕራፍ 50 አንቀጽ 16

እንዲሁም አንድ የ ነብዩን ሙሀመድ ንግግራቸውን ለመጨመር
ኢብኑ ዐባስ (ረዐ) እንዲህ አሉ – “አንድ ቀን ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጀርባ እየነዳሁ እንዲህ አለ -“ አንተ ልጅ ሆይ ፣ አላህን አስብ እሱ ይጠብቅሃል።አላህን ፍሩ ከአንተም ጋር ታገኘዋለህ። ስትለምኑ (ለምንም ነገር) ከአላህ ለምኑት ፤ እርዳታ ከፈለጋችሁም ከአላህ እርዳታ ጠይቁ። በአት-ቲርሚዚ

ስለዚህ እኛ ሙስሊሞች የምናመልከው አንዱ እና የሁሉም ፈጣሪ የሆነውን አምላክ ብቻ ነው።
ጥሩ ነገር ያልኩት ማንኛውም ነገር ከአላህ ነው ፣ ስሕተት ሁሉ ከኔ ነው ፡፡

