ከቃሉ እንደምንረዳው የተለያዩ የእምንት እና የሃይማኖት ብዱኖች እውነት ነው ብለው የሚያምኑትን ነጥቦች እና ማስረጃዎችን በማንሳት የሃሳብ ልውውጥ፤ ምክክር ፤ ሙግት ማከናወን ማለት ነው።
እንደሚታወቀው ሀገራችን የብዙ ሀይማኖት ተከታዮች መገኛ ናት በተጨማሪም ለብዙ የ አለማችን ህዝቦች ተምሳሌት በሚሆን መልኩ የመከባበር የ መቻቻል እሴቶችን የያዙ ህዝቦች መገኛ ናት። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን እንድኛችን የሌሎቻችን ሃይማኖት እና እምነት ለማክበር እና የተከታዮቹን ስሜት ላለመንካት በሚል ከራሳችን ሃይማኖት እና እምነት ውጪ? ስለሌላው ያለን እውቀት በጣም ትንሽ እና አንዳንዴም ይባስ ብሎ የተሳሳተ ነው።
ይህንን መቅረፍ የምንችለው በ አንድ እና አንድ መንገድ በቻ ነው እሱም አካባቢያችን ያሉ የሌላ ሃይማኖት እና እምነት ተከታዮችን ሃይማኖት/እምነት ማወቅ እና መረዳት ስንችል ብቻ ነው። ይህንን ማደረግ ምንችለው ደግሞ እኒህን የእምነት ተከታዮችን “ስለሃይማኖታቹ እንዴት ማወቅ እና መረዳት እችላለው” ብለን ስንጠይቅ ነው። አሁን እንዚህ ጋር ለምን የሚል ሃሳብ ብዙዎች ላይ ይነሳል በሁለቱም በኩል ማለትም “የራሴ ሃይማኖት እያለኝ የሌላው ለምንድን ነው ማወቅ የሚያስፈልገኛል?”የሚል ሲሆን ሌላኛው እና ብዙግዜ ይነሳል ብዮ ማለስበው ደግሞ ”ስለ እኔ ሃይማኖት ለምን ማወቅ ፈለግክ?” ነው።
“የራሴ ሃይማኖት እያለኝ የሌላው ለምንድን ነው ማወቅ የሚያስፈልገኛል?”
ይህ ጥያቄ በወስጡ አንድ ሃሳብ ይዛል ይህም እየተከተልኩት ያለውት ሃይማኖት እውነት ነው የሌላው ደግሞ እውነት አይደለም የሚል አንድምታ ነው። ግን ጭፍን እምነት ከሌለን በስተቀር የሌላው እውነት አይደለም ከማለታችን በፊት በቅድሚያ ምንድነው እምነቱ ብሎ ማወቅ እና መጠየቅ ተገቢ ነው።
በተጨማሪም እየተከተልኩት ሃይማኖት እውነት ክሆነ ይህን ጥያቄ በመጠየቅ የምታተርፈው ነገር ባለህ እምነት ላይ የበለጠ የሆነ ጥንካሬ እንጂ ጥርጣሬ አይሆንም።
በተጨማሪም ስለ ሌሎች የምንጨነቅ እና የምናስብ ከሆነ ስለ ህይወታቸው የማወቅ ፍላጎት ሊይድርብን መገባቱ ተፍጥሮአዊ ነው በመሆኑም የ አብዛኛዎቻችን ህይወት በምንከተለው የሃይማኖት እና እምነት የተቃኝ ነው።
ስለዚህም የመከባበር፤ የመቻቻል እሴቶችንን አጠናክረን መቀጠል የምንችለው እንድኛችን የሌሎቻችን ሃይማኖት እና እምነት ለማክበር እና ስሜት ላለመንካት በሚል ስለሌላው ያለንን ዝቅተኛ እና የተሳሳተ እውቀትን ይዞ መቀጠል ሳይሆን እርስበርሳችን በመጠያየቅ እና ሀይማኖታዊ ውይይቶችን በማደረግ ስንችል ነው።
”ስለ እኔ ሃይማኖት ለምን ማወቅ ፈለግክ?”
አንድ ሰው እየተከተለው ያለውን ሃይማኖት እውነት ነው ብሎ የማመን በትንሹ የሚጠበቅ መስፈርት ነው ስለዚህም እውነት ነው ብሎ የሚከተለውን ሃይማኖት ለማወቅ ለሚፈልግ ግለሰብ በተቻለው አቅም ለማስረዳት ፍላጎት ሊይድርበት መገባቱ ተፍጥሮአዊ ነው ስለዚህ በየተኛውም መንገድ ብናየው ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን።
እንደስልምና አስተምህሮ፦
ይህን ሃሳብ የሚከተሉት የቁርአን አንቀጾች ይስተምራሉ፦

«ገነትንም አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን የኾነ ሰው እንጂ ሌላ አይገባትም» አሉ፡፡ ይህቺ (ከንቱ) ምኞታቸው ናት፡፡ «እውነተኞች እንደኾናችሁ አስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡
(ምዕሪፍ 2 አንቀፅ 111)
በዚህ አንቀፅ እንደምንረዳው አላህ (ሰ.ወ) አይሁድ እና ክርስቲያኖች ለሚይምነት እምነት ማስረጃ አምጡ በላቸው በማለት በቀጥታ ነብዩን(ሱ.አ.ወ) ሲያዛቸዋል በተዘዋዋሪም እኛን ከእነዚህ የእምነት ብድኖች ጋር በማስረጃ የተመሰረተ ውይይት እንድናደርግ ያስተምረናል ::
በተጨማሪም

«አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ፤ (ቅኑን መንገድ) ትመራላችሁና» አሉም፡፡ «አይደለም የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን፤ ከአጋሪዎችም አልነበረም» በላቸው፡
(ምዕሪፍ 2 አንቀፅ 135)
በዚህ አንቀፅ እንደምንረዳው አይሁዶችም ሆኑ ክርስቲያኖች የኛን መንገድ ተከተሉ የኛ ነው እውነት ብለው ይጣራሉ እኛም ለዚህ የስህተት እና የጥመት ጥሪ በማስረጃ እና በ እውነተኛ አመክኒዮ በመደገፍ ስህተታችውን ልናሳያችው እንደሚገባነው።
ብዙ አንቀጾችን እና ሀዲሶችን በማንሳት ሀይማኖታዊ ውይይት የሚለውን ሃሳብ መደገፍ ይቻላል።

true