በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው ።
አምላክ ባይሆን ሙታንን ያስነሳልን? አምላክ ባይሆን ኑሮ ለ አይነ-ስውራን ብርሀን ይሰጣልን? አምላክ ባይሆን ኑሮ ለምጽምን ያነጻልን አምላክ ባይሆን ኑሮ?…አምላክ ባይሆን ኑሮ ….? የ ክርስትና ሀይማኖት መምህራን ሳይቀሩ እንዲህ ሲሉ መስማት የተለመደ ሁኖል። እስቲ ይህንን አመክንዪ ምክንያታዊ በመሆን እንፈትሸው።
በመጀመሪያ ትዐምራቶች በጠቅላላ የሚሰጡት ከፈጣሪ ነው እንጂ ተዐምራቱን የሚፈፀመው ነብይ እና አካል ከራሱ የሚፈጸመው አይደለም ይህንንም እውነታ እራሱ እየሱስን እንደማሳያነት በማቅረብ እንመለከታለን ::
ኢየሱስ የሚያደርጋቸው ታምራት ሁሉ በፈጣሪው ስም እንጂ ከራሱ ምንም ማድረግ እንደማይችል ሲነግረን እንመለከታለን፦
ዮሐንስ 10፥25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም ”እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል”።
ዮሐንስ 5:30 *”እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም”፤
እዚህ ጋር ማስተዋል የሚኖርብን እንዴት አምላክ የሆነ አካል “ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም” ይላል? እንዴትስ አምላክ የሆነ አካል በሌላ ማንነትና ተመርኩዞ ተዓምር ያደርጋል? በዚህም አያበቃም ጭራሽኑ እየሱስ የሚያደርጋቸው ሥራዎች ከፈጣሪ በጸጋ ያገኛቸው እንደሆኑ እና ለእርሱ መልክተኛነት ማስረጃ እንደሆኑ ደጋግሞ ሲናገር እንመለከታለን ፦
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደላከኝ” ስለ እኔ ይመሰክራልና።
እንዲሁም
ዮሐንስ 11፥42 አላዛርን ከሞት ካስነሳ በሆላ እንዲህ አለ ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ አወቃለሁ፤ ነገር ግን ”አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ” በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።
ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራቶች ፣ አልላኬ የሚለው አካል በኢየሱስ በኩል ያደረገው ነው።
የዩሃንስ ወንጌል 20:17 ኢየሱስም፣ “ገና ወደ አብ ስላላረግሁ፣ አትንኪኝ፤ ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፣ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ’ ብሏል ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።
እንዲሁም
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤
ስለዚህ አንባቡ ሆይ ተዓምር የተሰጠውን ሳይሆን ተዓምር ሰጭውን አምልክ ።
የፈጣሪያችን ንግግር የሆነውን ቁርዐንም በምንመለከትበትም ግዜ
ታምር ከአላህ ለነቢያር የተሰጣቸው ስጦታ እንደሆነ በግልጽ ይነግረናል፦
(ምዕራፍ 2፥87)

ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክተኞችን አስከታተልን፡፡ *የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው*፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው።
ሌላው ትልቁ ስህተት “የ እየሱስ ተዐምራት መፈጸም ፈጣሪ ነቱን ያሳያል” በሚለው አስተሳሰብ ላይ ተዐምራት እንኮን አምላክነት ማረጋገጫ ሊሆን ቀርቶ እውነተኛ ነብይነትን እንካን ብቻውን ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም ምክንያቱ ተዓምራቶችን የውሸት ነብዮችም ሊፈጽሙት ስለሚችሉ ነው።
ዘ-ዳግም 13:1–3 ላይ እንዲህ ይላል ።
ነቢይ ወይም ሕልም ዐላሚ ከመካከልህ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፣ የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፣ “አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው” ቢልህ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁ ነውና፣ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም ዐላሚውን አትስማ።
እንዲሁም ማርቆስ 13:22 ብንመለከትም ።
ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰትኞች ነብያት ይነሳሉና ፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንካ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅን ያደርጋሉ ።
ከ እስልምና አንፅርም አል መሲሁ ደጃል የመጨረቫው ቀን ሊቀርብ ሲል ሲመጣ እኔ ፈጣሪያቹ ነኝ በማለት ብዙ ተዓምራቶችን እንደሚያሳይ እናውቃለን እንግዲህ እንደዝህ ያሉ ሰውች ተዓምራትን የፈጣሪነት ማሳይ አድርገው የሚቆጥሩ ከመጀመሪያዎቹ ተከታዮች ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ከባድ አይደለም።
ይህንን ከተመለከትን በመጨረሻ ደግሞ እውን እየሱስ ሰራቸው ተብለው የተቀመጡት ትዐምራቶች ከሱ በፊት በመጡት ነብያቶች ያልተሰሩ ናችው ወይ ብለን ብንጠይቅ መልሱ አይደለም ነው ። የተወሰኑትን እንደማሳያነት እነመልከት
እየሱስ ሙታንን ማስነሳቱን ዩሃንስ 11:41-44 ላይ ተጽፎ እናገኝዋለን ኤልያስም ሙታንን ማስነሳቱን በ 1 ነገሥት 17:19:23 ላይ ተጽፎ እናገኝዋለን።
አንባቢ ሆይ ኤልይስም አምላክ ነው ብለህ ታምናለህን? ካልሆነግን የኤልያስን አምላክ አምልክ ።
እየሱስ ለምጽምን ማንጻቱን ሉቃስ 17:12-14 ትፅፎ እናገኝዋለን ኤልሳዕም ለምጽም ሲያጽዳ 2 ነገሥት 5:7-14 ተጽፎ እናገኝዋለን።
አንባቢ ሆይ ኤልሳዕም አምላክ ነው ብለህ ታምናለህን? ካልሆነግን የኤልሳዕን አምላክ አምልክ።
እየሱስ አይነ ስውሩን መፈወሱን ማርቆስ 10:50-52 ተጽፎ እናገኝዋለን ኤልሳዕም አይነ ስውሩን ሲፈውስ 2 ነገሥት 6:17-14 ተጽፎ እናገኝዋለን።
አንባቢ ሆይ ኤልሳዕም አምላክ ነው ብለህ ታምናለህን? ካልሆነግን የኤልሳዕን አምላክ አምልክ።
ስለዝህ “እውን እየሱስ ክርስቶስ ተአምራትን መፈጸሙ አምላክ ያደርገዋልን?” ለሚለው ጥያቂ ምክንያታዊ መደምደምያችን የሚሆነው አያደርገውም ይሆናል ማለት ነው።
ጥሩ ነገር ያልኩት ማንኛውም ነገር ከአላህ ነው ፣ ስሕተት ሁሉ ከኔ ነው ፡፡

