You are currently viewing ሙስሊሞች ስለ “መጽሀፍ ቅዱስ” ምን ይላሉ?

ሙስሊሞች ስለ “መጽሀፍ ቅዱስ” ምን ይላሉ?

ሙስሊሞች ስለምንም ጉዳይ እና አቆም ሲጠየቁ በ ቁርዓን እና በ ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) ንግግሮች መመልከትን ይሻሉ።

ቁርዐንን አንብበን እንደምንረዳው ለቀደምት ነቢያቶች በተለያየ ጊዜያት የተሰጡ መጽሃፎቶች እንደነበሩ እናም እነዚህ ቅዱሳት መፅሃፍቶች እውነት እና ከ ፈጣሪ ለህዝቦቹ መመሪያ እና ብርሀን አድርጎ እውርዶቸው እንደነበር እንረዳለን ።  ለምሳሌ ቶራህ ለ ሙሴ ዘብር ለ ዳዊት ኢንጂል ለ ኢሳ እንዲሁም ሌሎችም። ሲቀጥልም እነዝህን መፅሀፎች የመጠበቁን ሀላፊነት በእነዚያ መፅሀፍ በተሰጣቸው ሕዝቦች  ላይ ተጥሎ ነበር።

ምዕራፍ (5:44)

የቀደሙት ነብዪች ህዝቦሽ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጠበቅ ተፈትነዋል፣ ነገር ግን ይኅህን ፈተና ወድቀዋል ምክንያቱም በሰው ሰራሽ ጭማሪ እና መቀነሶች የተሰጣቸውን መጽሀፍ  በመበርዝ እንዲሁም በመለወጣቸው ምክንያት።  ከእነዚህ የቀደምት ቅዱሳት መጻህፍት አንዳቸውም በቀድሞ ይዞታቸው ሙሉ በሙሉ አይገኙም ።

(ምዕራፍ 2:79)

(ምዕራፍ 3:78)

የቀደምት ቅዱሳት መጻህፍት አንዳቸውም በቀድሞ ይዘታቸው ሙሉ ለሙሉ እንደማይገኙ ከተረዳን ።ነቢዩ ሙሐመድ ለሰው ልጆች ሁሉ የተላኩ የመጨረሻው ነብይ ስለሆኑ ከርሳቸውም በኋላ የሚመጣ ነቢይ ስለማይኖር። ፈጣሪም አምላካችን አላህ  የመጨረሻውን ኪዳኑን ቅዱስ ቁርኣንን ላከ።  እንደ ያለፈው ቅዱሳት መጻሕፍት በተመሳሳይ መልኩ በሰዎች እንዳይበረዝ ለማድረግ ቅዱስ ቁርኣንን የመጠበቅን ሀላፊነቱን የወሰደው ፈጣሪ እራሱ ሆነ የመጨረሻዎቹ ህዝቦችን ወደ ትክክለኛውን መንገድ የሚመራውን ይህን ቁርኣንን ብቻ የመከተል አደራ ተሰጥቶታል። ፈጣሪም እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ይህንን ንግግሩን ለመጠበቅም  በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ግልፅ የሆነ ቃል ኪዳን ገብቷል።

{ምዕራፍ 9:15}

ቁርአን የመውረድ አንድ ምክንያት የቀድሞ መለኮታዊ መፅሀፍቶችን የሚያረጋግጥና የሚያርም ፍፁም የፈጣሪ ቃል ስለሆነ ነው ። የቅዱስ ቁርዓን ሌላ መጠሪያ ስሙ አል-ፉርቃን  ነው ትርጉሙም መስፈርት ማለት ነው፡፡ የሚያመላክተውም ቁርአን ሁሉ ነገር  የሚዳኝበት ወይም የሚወሰንበት መርህ ወይም መስፈርት መሆኑን ነው። ስለዚህም ቁርአን ትክክልና ስህተቱን እውነት እና ውሸቱን የሚያጣራ መስፈርት ነው።

ምዕራፍ 5:48

ስለዚህ ይህ ቁርአን እውነቱን ለመመስከር ውሽቱን ደግሞ ለማጋለጥ የተላከ ነው። አሁን በተለያዩ የክርስቲያን denomination እና በአይሁድ sects’ እጅ የሚገኙት መጽሃፍቶች ውስጥ የቀሩ የእውነት ዱካዎች ቢኖሩም፣ በመጀመሪያ ቅርጻቸው የቆሙ አይደሉም።

በመሆኑም ባልተበረዘው እና በተጠበቀው የአላህ ንግግር እነዚህን የቀደምት መፅሀፍትን ምንመዝን ይሆናል እነዝህ መፅሀፍት ውስጥ በቀጥታ ከቁርአን ጋር የሚጋጭ ሃሳቦች ካሉ አንቀበለውም ምክንያቱም እነዝህ መፅሀፍት የሰዋች ጣልቃ ገብነት እንዳለ በግልፅ ማሳየት ስለምንችል ። በተቃራነው ከቁርአን ጋር የሚስማማ መልክት ሚያስተላልፉ ከሆነ እንቀበለዋለን ። እንዲሁም በቁርአን በዝምታ የታለፈ ግዳይ ከሆነ እውነት ነው ወይም አይደለም ከማለት እነወሰናለን።

በዝህ አቆም ላይ የሚነሳው ተቃውሞን እንመልከት  ፦ 

“Cherry picking fallacy”

አንድ ሰው አቋሙን በሚደግፉ ማስረጃዎች ላይ ብቻ ሲያተኩር እና ከእሱ ጋር የሚቃረኑ ማስረጃዎችን ችላ በማለት የሚከሰት አመክክኒዋዊ ስህተት/ Fallacy ነው። ይህንን መሰረት አድርገው ክርስቲያን እና አይሁድ ወገኖቻችን እንዱህ ሲሉ ይደመጣል” የተመቻችሁን ብቻ እየመረጣችሁ የማይመቻችሁን ደግሞ ተበርዛል ተለውጣል ትላላቹ፡”” ይላሉ””

ይህንን ተቃውሞ objectively አሁን ያለው ሂብሩ ባይብልን ለ ሙሴ የተሰጠው ቶራህ ነው ልንለው እንደማንችል በተመሳሳይም አሁን ያሉት ወንጌሎች ወይም የአዲስ ኪዳን መፅሀፍቶች ለ እየሱስ የ ወረደለት መለኮታዊ መልዕክት ነው ልንላቸው እንደማንችል በማስረጃ ማቅረብ ቀላል ነው።( ወደፊት የሚለቀቁ ጹሁፎችን ተምልከቱ)

“ታዲያ እናንተ ሙስሊሞችን ለምንድነው ከማታያምኑበት መጽሀፍ የምትጠቅሱት ? ”  የሚል ትችትን ደግሞ እንመልከት

ከላይ ሲታይ ትክክለኛ ምክንያት ቢመስልም ኢ- አመክንዮአዊ አቆም ነው ይህንንም ለማስረዳት አንድ analogy/thought experiment/እንመልከት።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፈጣሪ አሉ ብሎ ከሚያምን አንድ ሂንዱ ጋር እየተነጋገርኩ ነው እንበል። እንዲህም ብዬ ጠየቅኩት ለምን በአንድ ፈጣሪ አታምንም በቫዳስህ (በአንተ ቅዱሳን መጻህፍትህ)  ውስጥ እኮ ፈጣሪ አንድ ነው፤ እንደ እርሱ ያለ ምንም የለም፤ ለእግዚአብሔርም ምንም ሐውልት የለም ይላል ብለው እና ።

ያቀረብኩትን ክርክር ሲሟገት ዞር ብሎ አንዲት እመበለቶች ከሞተ ባላቸው ጋር መቃጠል እንደሌለባቸው የማታምኑ ከሆነ ለምን ከመፅሃፉ ትጠቅሳለህ? ቢለኝ

አብደሃል ወይ ነው ምለው ምን አገናኝ

እኔ ያደረግኩት የሱን standard of evidence and standard of truth በመጠቀም ያዘው አቆም እና እምነት የተሳሳተ እንደሆነ ነው ያሳየሁት። ይህን ለማድረግ ደግሞ የተጠቀምኩት source ሙሉ በሙሉ based on my standard /መስፈርት reliable information መሆን አይጠበቅበትም as long as he accept it to be reliable.

ለምሳሌ፦ አንድ ክርስቲያን/ሂንዱ/አይሁዳ አንድ ሙስሊም አልኮል ሲጠጣ አይቶ ቁርኣን አልኮልን መጠጣት ይከለክላል ስለዚህ ሓጢያት እየሰራህ ነው ቢል። ይህ ክርስቲያን/ሂንዱ/አይሁድ  ቁርኣንን የፈጣሪ ቃል ነው ብሎ ስለተቀበለ ነው ማለት አይደለም ይልቁንም የሰውየውን ማስረጃ እና መስፈርት በመጠቀም በድርጊቱን ወይም አቆሙ ላይ ትችት ሰነዘረ እንጂ።

Leave a Reply